Showing posts with label የኮምፒውተር ጥያቄና መልሶች. Show all posts
Showing posts with label የኮምፒውተር ጥያቄና መልሶች. Show all posts

Friday, December 6, 2013

የኮምፒውተር ጥያቄና መልሶች: ኮምፒውተሬ አማርኛ አይጽፍም፡፡ ምን ላድርግ?

ጥያቄ
ኮምፒውተሬ አማርኛ አይጽፍም፡፡ ምን ላድርግ?

መልስ
ኮምፒውተር ላይ አማርኛ ለመጻፍ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ 
    ለምሳሌ፡ ፓወር ግዕዝ፣ ቪዥዋል ግዕዝ፣ አብነት(ኤቢኔት) ግዕዝ ከታዋቂዎቹ መካከል ይገኙበታል፡፡
ከእነዚህ ሶፍትዌሮች  መካከል አንዱን ጭነህ/ቀድተህ መጠቀም ትችላለህ፡፡

ወይንም ደግሞ ኢንተርኔት ላይ የተለያዩ አማርኛ በቀላሉ እንድትጽፍ የሚያስችሉህ መካነ-ድሮች አሉ፡፡
የምትጽፈውንም ጽሁፍ ቀጥታ ወደ ፌስቡክና ሌሎች ማኅበራዊ መካነ-ድሮች መላክ ትችላለህ፡፡

ለምሳሌ
http://www.amharickeyboard.com/
http://www.typeamharic.com/

ጥያቄዎን ይጠይቁ!
ላይክ ያድርጉ!
ሼር ያድርጉ!
ብዙ ጥያቄ ከመለሱ የዚህ ፌስቤክ ገጽ አስተዳዳሪ ይሆናሉ!

www.facebook.com/compqa

የኮምፒውተር ጥያቄና መልሶች: ኮምፒውተሬን ስዘጋው በጣም ስለሚቆይ የማስነሻውን ቁልፍ ይዤ ነው የማጠፋው፡፡ እባካህ መፍትሔ ካለ፡፡


ለብዙ ኢትዩጵያውያን የሚጠቅም እንዲሆን መልሱን በአማርኛ እመልሳለሁ፡፡

ጥያቄ
When I turn of my laptop using start>shutdown, it gets stacked and stays like that and I have been using a long press to shutdown my laptop. Do you have a solution please?

በአማርኛ
ኮምፒውተሬን ስዘጋው በጣም ስለሚቆይ የማስነሻውን ቁልፍ ይዤ ነው የማጠፋው፡፡ እባካህ መፍትሔ ካለ፡፡

መልስ

ጥያቄህ ሰፋ ያለ ቢሆንም የሚከተሉት መፍትሔዎች የገጠመህን ችግር ይፈታልሀል፡፡
1. በቅርቡ የጫንከው ሶፍትዌር ወይም ሃርድዌር ካለ ችግሩን የፈጠረው ያ ሊሆን ስለሚችል ሶፍትዌሩን ወይም ሃርድዌሩን አስወግደህ ኮምፒውተሩን ለመዝጋት ሞክል፡፡ ከተሳካ ያ ሶፍትዌር ወይም ሃርድዌር ተመጣጣኝ (compatible) አይደለም ወይም አጫጫኑ ልክ ስላልሆነ ድጋሚ ሞክር ወይም ባለሙያ አማክር፡፡