ለብዙ ኢትዩጵያውያን የሚጠቅም እንዲሆን መልሱን በአማርኛ እመልሳለሁ፡፡
ጥያቄ
When I turn of my laptop using start>shutdown, it gets stacked and stays like that and I have been using a long press to shutdown my laptop. Do you have a solution please?
በአማርኛ
ኮምፒውተሬን ስዘጋው በጣም ስለሚቆይ የማስነሻውን ቁልፍ ይዤ ነው የማጠፋው፡፡ እባካህ መፍትሔ ካለ፡፡
መልስ
ጥያቄህ ሰፋ ያለ ቢሆንም የሚከተሉት መፍትሔዎች የገጠመህን ችግር ይፈታልሀል፡፡
1. በቅርቡ የጫንከው ሶፍትዌር ወይም ሃርድዌር ካለ ችግሩን የፈጠረው ያ ሊሆን ስለሚችል ሶፍትዌሩን ወይም ሃርድዌሩን አስወግደህ ኮምፒውተሩን ለመዝጋት ሞክል፡፡ ከተሳካ ያ ሶፍትዌር ወይም ሃርድዌር ተመጣጣኝ (compatible) አይደለም ወይም አጫጫኑ ልክ ስላልሆነ ድጋሚ ሞክር ወይም ባለሙያ አማክር፡፡
2. ዊንዶውስ አፕዴት (የዊንዶውስ ማደሻ) ከኢንተርኔት የተለያዩ አፕዴትስ (ማደሻዎች፣ ማስተካከያዎችና ጭማሪዎች) ከቀዳ በኃላ ኮምፒውተርህን ስትዘጋ እና ስትከፍት ወደ ዋናው የኮምፒውተርህ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ስለሚቀዳቸው እስኪጨርስ መጠበቅ ይመከራል፡፡ ያለበለዚያ ኮምፒውተርህ አልከፍትም ብሎም ሊያስቸግርህ ይችላልና፡፡
3. ሲስተምህ ላይ ስህተት (error) ካለ ለማረጋገጥ የሚከተለውን መንገድ ተጠቀም፡፡
Start ላይ ክሊክ አድርግ
cmd ብለህ ጻፍ
cmd የሚለው ላይ ራይት ክሊክ አድርግና የሚለውን ምረጥ
አሁን sfc /scannow ብለህ ጻፍ (በ sfc እና /scannow መካከል ስፔስ ወይም ክፍተት አለ)
4. ከላይ የተጠቀሱት አማራጮች ካልሰሩ
ቻርጀሩን ነቅለህ ባትሪው እስኪያልቅ ከጠበቅክ በኃላ ባትሪውን ነቅለህ መልሰህ ሰካው፡፡
ጥያቄዎን https://www.facebook.com/compqa ይጠይቁ!
ላይክ ያድርጉ!
ሼር ያድርጉ!
ብዙ ጥያቄ ከመለሱ የዚህ ፌስቤክ ገጽ አስተዳዳሪ ይሆናሉ!
No comments:
Post a Comment