Thursday, January 9, 2014

በነገራችን ላይ አስተሳሰብሽን ግን ወድጄልሻለሁ!

አስተማሪዋ ክፍል ውስጥ እያስተማረች ነው፡፡ በመሃል ትንሹ ቤቢ አትኩሮቱ ትምህርቱ ላይ እንዳልሆነ ስላየች የሚከተለውን
ጥያቄ ጠየቀችው
ቲቸር፡- “3 እርግቦች አጥር ላይ ብታይና አንዷን በጥይት ብትመታት ስንት ወፎች ናቸው አጥሩ ላይ የሚቀሩት?”
ትንሹ ቤቢ፡- “ምንም አይቀርም፡፡”
ቲቸር፡- “ለምን?”
ትንሹ ቤቢ፡- “ምክንያቱም የጥይቱ ድምፅ ሁሉንም ስለሚያስደነግጣቸው ሁሉም አይኖሩም፡፡”
ቲቸር፡- “አይ እንደሱ አይደለም፡፡ መልሱ 2 ነው እሺ፡፡ ግን አስተሳሰብህን ወድጄልሃለሁ፡፡”

በዚህ ጊዜ ትንሹ ቤቢ በጣም ተናደደ፡፡ ስለሆነም በተራው ይህንን ጠየቀ፡፡
ትንሹ ቤቢ፡- “እሺ 3 ሴቶች ከአይስክሬም መሸጫ ሱቅ አይስክሬም ገዝተው ወጡ እንበል፡፡
ከዛ አንደኛዋ አይስክሬሙን በቅብጠት ትልሰዋለች፣
አንደኛዋ ደግሞ በእርጋታ አይስክሬሙን ትመጠዋለች፣
ሦስተኛዋ ደግሞ አይስክሬሙን በችኮላ ትነክሰዋለች፡፡
እና ከሦስቱ መካከል ትዳር ያላት የትኛዋ ናት?”

ቲቸር፡- “አይስክሬሙን በእርጋታ የምትመጠው ናታ፡፡”
ትንሹ ቤቢ፡- ፈገግ ብሎ “ተሳስተሻል፡፡”
ቲቸር፡- “ለምን?”
ትንሺ ቤቢ፡- “ምክንያቱም ከሦስቱ መካከል ትዳር ያላት በእርጋታ አይስክሬም የምትመጠው ሳትሆን እጇ ላይ የትዳር ቀለበት ያረገችው ናት እሺ፡፡ በነገራችን ላይ አስተሳሰብሽን ግን ወድጄልሻለሁ፡፡”

No comments:

Post a Comment